የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዲጅታል የባንክ ሥርዓቱ ላይ ባጋጠመው ችግር ምክንያት ህገወጥ ግብይቶች እንደተፈፀሙበት አስታወቀ።
ባንኩ ባወጣው መግለጫ ሌሊት ላይ አጋጥሟል ባለው ችግር የዩንቨርስቲ ተማሪዎች መሳተፋቸውን ገልጾ በአሁኑ ወቅትም በሕገ ወጥ መንገድ የተወሰዱ ገንዘቦችን እያስመለሰ መኾኑን አስታውቋል።
እንዲህ ያለ ችግር ሊያጋጥም እንደሚችል የተናገሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ሰውአለ አባተ፣ ችግሩን ለመለየት ተጨማሪ ምርመራ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል። ክስተቱ ብሄራዊ ባንክን ጨምሮ ሁሉም የፋይናንስ ተቋማት የአስራር ሥርዓቶቻቸውን እንዲፈትሹ ትምህርት የሚሆን ነውም ሲሉ ተናግረዋል፡፡